Skip to main content

2022-2023 MCPS

የትምህርት አመት መጨረሻ ማጠቃለያ

ከሱፐርኢንተንደንት ዴስክ
Dr. Monifa B. McKnight

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ሌላ አንድ የትምህርት አመት ስናጠናቅቅ በጉዟችን የተወጣናቸውን ስኬቶቻችንን፣ እድገቶቻችንን፣ እና አይበገሬ መንፈሳችንን ማክበር አለብን። በእነዚህ ዘጠኝ ወራት ውስጥ አንድ ሶስተኛውን  ትምህርት ቤቶች በጎበኘሁበት ወቅት፣ ተማሪዎቻችን በጥልቅ ሲሳተፉ እና ሲማሩ አይቻለሁ፣ ስለዚህ በቀጣይነት ከተጠበቀው በላይ ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እና ድጋፍ የሰጡትን ልዩ መምህራን ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ከአሁን በኋላ የስኬት መንገዳቸውን የሚቀጥሉ 12,000 የሚጠጉ ተማሪዎችን የምርቃ ሥነ ሥርአት በቅርቡ አክብረዋል። ለተመራቂዎቻችን፥ ለዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! በለውጥ ውስጥ የመጓዝ ጽናትን፣ብቃትን እና መላመድን አሳይታችኋል። በስኬቶቻችሁ ኩራት ይሰማናል፥ እናም የወደፊት ዕጣችሁ ወዴት እንደሚመራችሁ ለማየት እንጓጓለን። 

ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናስብ በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ መሻሻል አሳይተናል። እኛስለ ተማሪዎች አፈጻጸም ሪፖርት ስናደርግ ሁሉም ተማሪዎች ሙሉ አካዳሚያዊ አቅማቸው ላይ እንዲደርሱ ለመደገፍ ያለንን እቅድ ደጋግመን ገልፀናል። የሜሪላንድ ስቴት የኮከብ ደረጃ ውጤት ያወጣ ሲሆን፣ በዚህ ውጤት መሠረት 92% የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ሶስት እና ከዚያ በላይ ኮከቦችን አግኝተዋል። እንዲሁም በኮሌጅ፣ በስራ እና በማህበረሰብ አገልግሎት ተማሪዎችን ወደ ስኬት መንገድ የሚመራቸውን መነቃቃት አሳይተናል። የተማሪዎች የደህንነት ጉዳዮች እና ዘረኝነትን እና አድሏዊነትን ለመቅረፍ ወሳኝ ስራ መሥራት እንዳለብን ለት/ቤቶች እና ለትምህርት ስርዓቱ መሪዎች ትኩረት የምንሰጠው ተግባር ሆኗል። 

በየትምህርት ቤቶቹ የደህንነት ጉዳዮችን መርምረናል፣ በየካምፓሱ አጠቃላይ አካላዊ ለደህንነት ጥበቃ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለመጨመር አዳዲስ እቅዶችን አውጥተናል፣ ከዚህ በተጨማሪ ዘረኝነት እና ጥላቻ የሚያስከትለውን ፈረጀ ብዙ ጉዳትና ተጽእኖ በሚመለከት በግልጽ ተነጋግረናል። የትምህርት ቦርዳችን የላቀ የአካዳሚክ እና የተግባር እቅዳችንን የሚወክል 2024 የበጀት ዓመት የሥራ ማስኬጃ በጀት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። 

የተማሪዎቻችንን እና የመምህራኖቻችንን አስደናቂ ስኬቶችን ከመመረቅ እስከ ስኮላርሺፕ እና የአካዳሚክ ሽልማቶችን መጎናጸፋቸውንስናከብር ትልቅ ደስታ ይሰማናል። የወደፊቱን ጊዜ ስናስብ፣ ኦገስት 28 ላይ የሚጀመረውን የትምህርት ቀን በጉጉት እንጠባበቃለን፥ እንደገና አንድ ላይ የምንሰበሰብበት፣ ለአዲሱ የትምህርት፣ የእድገት እና የስኬት አመት እንዲሆንልን ተዘጋጅተን እንጠብቃለን። 

ከአድማስ ባሻገር ፀሐያማ የሠመር ቀናት፡ ሠመር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ፣ አዳዲስ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችን በማሰስ እና የጀብድ ተግባራት ላይ በመሳተፍ፣ ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ እውቀት የምትሸምቱበት ጊዜ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኛ ቁርጠኛ አስተማሪዎች እና አስተዳዳሪዎች ለሚቀጥለው የትምህርት አመት በዝግጅት ላይ ይቆያሉ። ትምህርት በሚጀመርበት ቀን ሁላችሁንም እስክንገናኝ በጉጉት እንጠብቃለን! 

ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ ማዕከል ለ2023-2024 ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርእይ የቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ማድረግዎን ያስታውሱ። ከማናቸውም ጊዜ የበለጠ ትልቅ እና የተሻለ ይሆናል። እኛ ሥራችንን እንወዳለን እናም ከእርስዎ ጋር አንድ ላይ ተባብረን እንሠራለን።

ከመልካም ወዳጅነት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክናይት
Superintendent of Schools የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት

በጣም ጉልህ ስኬቶች

የትምህርት ቤቶቻችን ዲስትሪክት ባከናወናቸው በርካታ ስኬቶች ታላቅ ኩራት ይሰማኛል። የተማሪዎችን ውጤት ከማሻሻል እና ከማሳደግ ጀምሮ ኢላማ እስከተደረገው በጀት የማሳካት ጥረቶች፣ ሠራተኞችን ለመመልመል እና ለማቆየት የሚረዱ ኮንትራቶች እና በርካታ የትምህርት ቤት ደህንነት ጥበቃ ማሻሻያዎች፣ ዘንድሮ አስደናቂ እርምጃ እና እድገት ታይቷል።

ይህ ሁሉ ስኬት ትጉህ መምህራኖቻችን፣ ሰራተኞቻችን እና አስተዳዳሪዎቻችን እንዲሁም የማእከላዊ ጽ/ቤት ባለራዕይ አመራሮች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ማሳያ ነው። በዚህ ክፍል፣ ባለፈው የትምህርት አመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ያከናወኗቸውን ጉልህ ስኬቶች አቀርባለሁ። በትምህርት የላቀ ደረጃ ለመድረስ ከፍ ያለ ጥረት ማድረግ እና ለስኬት አዳዲስ መመዘኛዎችን ማውጣት የዘወትር ግቤ ነው። የወደፊቱን ጊዜ ስንመለከት፣ ዲስትሪክታችን እንደሚያብብ እና እድገቱን እንደሚቀጥል እርግጠኛ ነኝ።


የተማሪዎች የትምህርት አፈጻጸም

የተማሪዎች ትምህርት አፈጻጸም ውሂብ ሁል ጊዜ ተማሪዎቻችን በት/ቤት ውስጥ ምን ያህል ጥሩ እንደሚሠሩ ጠቃሚ ግንዛቤ ይሰጣል። በተለያዩ አጋጣሚዎች ተማሪዎቻችን የአካዳሚክ ስኬት እያሳዩ እንዳሉ እና ጥረታችንን ማስተካከል ያለብንን ሁኔታዎች የሚጠቁሙ ቁልፍ መረጃዎችን ለትምህርት ቦርድ እና ለሁሉም ቤተሰቦች ሪፖርት አድርገናል። 3ኛ እና 9ኛ ክፍል የሂሳብ እና የሊተርሲ ውጤቶች መሻሻልና ማደጉን የሚያሳዩ የትምህርት መረጃዎችን ተመልክተናል፣ነገር ግን ይኼው ተመሳሳይ መረጃ መካከለኛ ደረጃ ላይ በሚገኙ ክፍሎች ትኩረት መስጠት እንዳለብን ያሳያል። እንዲሁም 92% ትምህርት ቤቶቻችንን ሶስት ኮከብ ወይም ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ከስቴቱ ተቀብለናል። በዚህ ክፍል ውስጥ የዚህን በጣም አስፈላጊ ሥራ ምሳሌዎችን አካፍላለሁ።

የአመቱ አጋማሽ የትምህርት ማዕቀፍ ማስረጃ በተማሪዎች ትምህርት የመቅሰም አፈጻጸም ላይ የተገኘውን ውጤት እና መሻሻል የሚያስፈልጋቸውን ዘርፎች ያሳያል

የመካከለኛው ግማሽ አመት የትምህርት ማዕቀፍ ማስረጃ የተማሪዎችን የስራ አፈፃፀም የሚስብ ዘገባ የቀረበ ሲሆን፣በዚህም ጠንክሮ መሥራትን እና ትጋትን የሚያንፀባርቁ ከፍተኛ ፋይዳዎችን አሳይቷል። እነዚህን ስኬቶች ባከበርንበት ወቅት፣ እያንዳንዱ ተማሪ ወደ ሙሉ አቅሙ እንዲደርስ የሚፈልገውን ድጋፍ እንዲያገኝ በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን መተለም አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበናል።

የሜሪላንድ ስቴት ሪፖርት ካርድ እንደሚያመለክተው 92% የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ባለ 3 ኮከብ እና ከዚያ በላይ የውጤት ነጥብ ደረጃ እንዳላቸው ያሳያል
የሜሪላንድ ስቴት ሪፖርት ካርድ አንድ በጣም አስደናቂ ስኬትን አሳይቷል።  በዚህ የስቴት የኮከብ ደረጃ አሰጣጥ ላይ አስደናቂ የሆነው ውጤት 92% የሚሆኑት የMCPS ትምህርት ቤቶች 3 ኮከብ እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፣ ይህም የአስተማሪዎችን፣ የተማሪዎችን እና የቤተሰቦችን ልዩ ቁርጠኝነት እና የትብብር ጥረት አጉልቶ ያሳያል። ይህ አስደናቂ ስኬት የትምህርት ጥራት እና በMCPS ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የማይናወጥ የልህቀት ፍለጎት በግልጽ ያሳያል።


2023-2024 የትምህርት አመት የስራ ማስኬጃ በጀት ጁን 6 ፀድቋል።

  • የሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ 2023–2024 የትምህርት አመት የስራ ማስኬጃ በጀት በአንድ ድምፅ አጽድቋል። ኦገስት 2022 የተጀመረው ሂደት ለት/ቤት እና ለቢሮ የሚያስፈልጉ ሰራተኞችን በመለየት፣ የተማሪ ምዝገባን በማቀድ እና የተማሪ አካዴሚያዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት እቅዶችን በማውጣት፣ የትምህርት ስርዓቱ የስራ ማስኬጃ በጀቱ ለአካዳሚክ እና ለተግባራዊ እንቅስቃሴዎች የላቀ እቅድ መኖሩን ያሳያል።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል የፀደቀው የባጀት መጠን ትልቅ ከሚባል የአመት ባጀት ጭማሪዎች አንዱ ሲሆን በወሳኝ ሁኔታ በወረርሽኙ ሳቢያ የተማሪዎችን የትምህርት መስተጓጎል ለማሟላት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አስፈላጊ መሆኑን እውቅና ይሰጣል። በጀቱ ዲስትሪክቱ ተመጣጣኝ ደመወዝ እንዲከፍል፣ የክፍል መጠን እንዳይጨምር እና በሁሉም ክፍሎች ሂሳብ እና ሊተርሲ የታለመ መስፈንጠርን ያካትታል፣ በተለይም መካከለኛ ክፍሎች ላይ ትኩረት የሚሹ ማሻሻያዎችን ያካትታል።


የሰራተኞች ኮንትራት MCPS በሥራ አቀጣጠር ተወዳዳሪ መሆኑን ያረጋግጣል።

MCPS በድርድር ኮንትራት አስፈላጊ ሰራተኞችን በመቅጠር ተወዳዳሪነቱን ያረጋግጣል

በዚህ ታሪካዊ የስራ ማስኬጃ በጀት ምክንያት MCPS እና ሶስቱ የሰራተኛ ማህበራት በተመጣጣኝ ደመወዝ እና የተሻሻለ የስራ ሁኔታ አዳዲስ የሁለት አመት ኮንትራቶችን ማጠናቀቅ ችለዋል። እነዚህ ስምምነቶች ሠራተኞች ለድስትሪክቱ የሚያመጡትን ዋጋ እና እውቀት ግንዛቤና እውቅና ይሰጣሉ። በአስፈላጊ ሁኔታ የተጨመረው የደመወዝ ክፍያ ዲስትሪክቱ ለተማሪዎቻችን ምርጡን እና ጥሩውን ሠራተኛ ለመመልመል እና ለማቆየት በሚያደርገው ጥረት ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቆይ ያስችለዋል።


ሠላም እና ደህንነት በሁሉም ትምህርት ቤቶች

MCPS የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ሠላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ የማይናወጥ ቁርጠኝነት አለው። ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የትምህርት ቤቶች ደህንነት ገጽታ ስንቃኝ፣ በዚህ አመት፣ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶቻችን መጸዳጃ ክፍሎች ውስጥ ድብድብ እና ህገ-ወጥ ዕፅ መጠቀምን የመሳሰሉ ተግዳሮቶች አጋጥመውናል። በምላሹ፥ እነዚህን ጉዳዮች አስቀድሞ ለመጠንቀቅ እና ለመፍታት የተሻሻሉ የደህንነት ጥበቃ እቅዶችን እና ስልቶችን ተግባራዊ እናደርጋለን፣ አንዱ የተሻሻለው ነገር የአደጋ ጊዜ የአሠራር ለውጦችን እንዴት እንደምናስተላልፍ ነው። ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት እና መዘግየት ለመረዳት ቀላል ወደሆነው "የቀለም ኮድ ስርዓት" ተሸጋግረናል። 

ይህ አመት ለመላው የMCPS ማህበረሰብ ሠላም፣ እና አጠቃላይ ደህንነት ትኩረት መስጠታችንን የምናረጋግጥበት ጠቃሚ አጋጣሚ ነበር። እነዚህን ስራዎች በብዙ የማህበረሰብ መልዕክቶቼ አካፍያለሁ።

የትምህርት ቤቶቻችን ሠላም እና ደህንነት መልእክት 

በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ያለው ሠላም እና ደህንነት በመከላከያ እርምጃዎች፣ አስፈላጊ ትብብር እና ለማንኛውም ክስተት አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የምንሰራው ወሳኝ የቅድሚያ ትኩረት ነው። የት/ቤት አካባቢዎቻችን ከደህንነት ስጋቶች ነፃ ሲሆኑ፣ ተማሪዎቻችን እና ሰራተኞቻችን ማተኮር እና በከፍተኛ ደረጃቸው/አቅማቸው መስራት ይችላሉ። በቅርቡ በዜናዎች ላይ የሚሰሙ ነገሮች/ታሪኮች በተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች የጭንቀት ሀሳቦችን እና ውይይቶችን ፈጥረዋል። ምንም እንኳን እነዚህ በቅርብ የተፈጠሩ አደጋኛ ክስተቶች ቢኖሩም፣ የእኛ 210 ትምህርት ቤቶች ደህንነትን ለመደገፍ በሰጠነው ትኩረት እና በመሰረትናቸው ሂደቶች የተነሳ ማህበረሰባችን ውስጥ ድህንነታቸው ከተጠበቁት ጥቂት ቦታዎች መካከል ይገኙበታል። ከፍተኛ ደረጃ ያለውን ደህንነት ለማስጠበቅ፣ ሁላችንም እንደ አጋሮች ሆነን መስራታችን አስፈላጊ ነው።

MCPS በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሠላም እና ደህንነት ያለው ቁርጠኝነት የተሻሻለ/UPDATE የመጸዳጃ ቤት እቅድን ያካትታል

MCPS አስተማማኝ፣ ፍትሃዊ እና ስኬታማ ትምህርት ቤቶች እንዲኖሩን ያለንን ቁርጠኝነት የሚዘረዝር ስለ ት/ቤት ሠላም እና ደህንነት አጠቃላይ ማዕቀፍ ፍኖተ ካርታ   አዘጋጅቷል። ይህንን ቁርጠኝነት ለመደገፍ፣ የትምህርት ስርዓታችን ተከታታይ የአፋጣኝ፣ የአጭር ጊዜ፣ እና የረዥም ጊዜ የሠላም እና ደህንነት ስልቶችን በመተግበር ላይ ነው። 

ይህንን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ትብብር ወሳኝ ነው፣ MCPS ከሰራተኞች፣ ከተማሪዎች፣ ከወላጆች እና ከሰፊው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት እየሰራ ነው፣ ይህም የሁሉንም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰቡ አባላት ፍላጎት ለማሟላት ካለን ቀጣይ "አሁን ሁላችን በጋራ /All Together Now" አካሄድ ጋር ይስማማል። የትብብር ማዕቀፉ የሚገነባው የታለሙ ግብዓቶችን፣ ክትትልን እና ተጠያቂነትን የመሳሰሉ አስፈላጊ ነገሮችን በመጠቀም ነው።

አዲስ የቀለም ኮድ ስርዓት የት/ቤት መዘጋትን፣ ዘግይቶ መከፈት ወይም ወደ ቨርቹዋል የትምህርት ቀን ለውጥ መደረጉን ያስተላልፋል

MCPS በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የአሠራር ለውጥ በሚያስፈልግበት ጊዜ ት/ቤት መዝጋት እና ወደ ቨርቹዋል ትምህርት መቀየሩን የሚያረጋግጥ ለህብረተሰቡ የማሳወቅ አሠራሩን አሻሽሏል። ሁኔታዎች ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ደህንነታቸው ያልተጠበቀ መሆኑን ሲታወቅ፣ በቀላሉ ለመረዳት የሚቻል፣ በቀለም የተጻፈባቸው (ከለር ኮድ) መልእክቶች የሚተላለፍባቸው ስድስት የአሠራር ሁኔታ አማራጮች አሉን። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

ቀጣይነት ያለው ጠቃሚ ሥራ

በዚህ ክፍል፣በትምህርት ተቋሞቻችን ውስጥ ዘረኝነት የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመከላከል የትምህርት ስርአታችን እንዴት ያለእረፍት ጥረት ሲያደርግ እና ሲሰራ እንደነበር ገልጫለሁ። በድርጊቶቻችን ላይ የሚታዩ ጭፍን ጥላቻዎችንና የጉልበተኝነት ድርጊቶችን በሚያጎሉ በርካታ አጋጣሚዎች ምክንያት፣ መግለጫ በመስጠት እና በርካታ የማህበረሰብ አጋሮችን በመጋበዝ ግንዛቤን ለማሳደግ በቁርጠኝነት ጥረት አድርጌአለሁ። ሁላችንም ይህ ጉዳይ የኛን የጋራ ትኩረት የሚፈልግ መሆኑን እና አሁን ለመናገር አስፈላጊ ጊዜ እንደሆነ ተነጋግረንበታል።  

ለሁሉም ተማሪዎች የበለጠ አሳታፊ እና ፍትሃዊ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር ተጨባጭ እርምጃዎችን እየወሰድን ያለንበትን የፀረ-ዘረኝነት የድርጊት መርሃ ግብር ትግበራ ጀምረናል። ለተማሪዎቻችን እና ለቤተሰቦቻችን ከትምህርት ክፍል ውጭ ስኬትን ለማግኘት ለኮሌጅ፣ ለስራ እና ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚያዘጋጃቸውን አስፈላጊ መመሪያ እና መረጃ የሚያገኙበትን መንገድ ለማሳየት ጓጉተናል። 

እነዚህ እርምጃዎች ቀጣይነት ያላቸው ጠቃሚ ስራዎች ከመሆናቸውም በላይ ለተማሪዎቻችን እና በአጠቃላይ ለማህበረሰባችን የተሻለ የወደፊት ሁኔታ ለመገንባት ያለን የቁርጠኝነት ጅምር ናቸው።


የሱፐርኢንተንደንት መልእክት፦ እኛ የምናወርሰው ምን ይሆን?

የተለያዩ የማህበረሰብ አጋሮቻችንን፣ የካውንቲ መሪዎችን እና ተማሪዎችን ወደ ሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጋበዝ ታሪክን፣ ሌሎች ሰዎችን በዘረኝነት እና በጥላቻ ሲያዋርዱ፣ ሲያንቋሽሹ እና ተፅእኖ ሲያደርጉ እርምጃ ለመውሰድ ያለንን የሞራል ግዴታ ተናግሬአለሁ። የእኔ ጥያቄ በፊትም ይሁን አሁን እና ሁል ጊዜ፥ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ማድረግ አለብን? የሚል ነው ይህንን በማህበረሰባችን ላይ ያለውን ተጽእኖ እና በከፍተኛ ደረጃ የመማር ችሎታን የሚገድብ እንቅፋት ለማስወገድ "ጥሪ ማድረግ" እና አብረን መሥራት አለብን።

ስለ ሁሉም አይነት ጥላቻ በግልጽ መነጋገር፡ፅሁፉን አንብቡእና ቪዲዮ ይመልከቱ።


ፀረ-ዘረኝነት የድርጊት መርሃ ግብር

ፀረ-ዘረኝነት የድርጊት መርሃ ግብር

ይህ ስርዓትአቀፍ ጸረ ዘረኝነት የድርጊት መርሃ ግብር ሜይ 11, 2023 ለትምህርት ቦርድ ቀርቧል። ዕቅዱ የተነደፈው ስርዓትአቀፍ የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ግኝቶች እና ምክረሃሳቦችን መፍትሔ ለመስጠት ነው።

የፀረ-ዘረኝነት ስርዓት የድርጊት መርሃ ግብር የድርጊት እርምጃዎችን እና የጊዜ ገደቦችን በማካተት በሶስት ክፍሎች የተደራጀ ነው፦

  • የስርዓትአቀፍ-ደረጃ እርምጃዎች

  • ጎራ-ተኮር እርምጃዎች

  • በትምህርት ቤት ደረጃ የሚወሰዱ እርምጃዎች

ዕቅዱ የተነደፈው በጣም የተገለሉ ተማሪዎቻችን ላይ ተጽእኖ የሚያፈጥሩ እንቅፋቶችን ለማስወገድ ነው። በሪፖርቱ የቀረበውን ዲስትሪክት አቀፍ የዘር ፍትሃዊነትና እኩልነት ራዕይ በተሳካ ሁኔታ ለማቀድ እና ለመተግበር የተቀናጀ አሰራር፣ ተጠያቂነት፣ ፍትሃዊነትን ያማከለ የአቅም ግንባታ፣ ቀጣይነት ያለው መረጃ መሰብሰብ እና የግንኙነት መተማመንን ማጎልበት ይጠይቃል።

የፀረ-ዘረኝነት ስርዓት የድርጊት መርሃ ግብር፦
English  / Español / French / አማርኛ / tiếng Việt / Portuguese / 中文 / 한국어

በኮሌጅ፣ በስራ እና በማህበረሰብ ውስጥ የተማሪዎች የስኬት መንገድ መግለጫ
በኮሌጅ፣ በሙያ እና በማህበረሰብ አገልግሎት ተነሳሽነት ለተማሪዎች የስኬት መንገድ ለማስተዋወቅ እየጓጓን ነበር። መንገዱ/pathway ተማሪዎችን ለእድሜ ልክ ስኬት ለማዘጋጀት ጠቃሚ መመሪያ ነው። አስፈላጊ የሆኑ አካዴሚያዊ ክንዋኔዎችን በማቅረብ ተማሪዎችን ያበረታታል፣ እንዲሁም ተማሪዎች በአካዳሚክ ተግባራቸው እንዲበለጽጉ፣ ትርጉም ላለው ስራ እንዲዘጋጁ እና ኃላፊነት እንደሚሰማቸው ዜጎች በንቃት እንዲሳተፉ ቁልፍ የሆኑ ብቃቶችን እና ልምዶችን ያስተምራል።


ጠንካራ የተማሪ የአእምሮ ጤና እና ደህንነት መተግበሪያ

MCPS Stronger Student / ጠንካራ የተማሪ አዕምሮ ጤና እና የደህንነት መተግበሪያ አሁን ይገኛል

ነፃ "MCPS Stronger Student" ሞባይል መተግበሪያ አሁን Apple እና Google Play መደብሮች ላይ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ለመተግበሪያው ሁሉንም የንድፍ፣ የግንባታ፣ እና የትኩረት ቡድን ባከናወኑ ተማሪዎች የተመራ ነው። መተግበሪያው የመድልዎ/ማግለል ክስተቶችን ሪፖርት ማድረግን ጨምሮ፣ የአደጋ ጊዜ ድጋፍ ምንጮችን እና ሌሎች የአዕምሮ እና የአካል ጤና እና ደህንነት ፍላጎቶችን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያቀርባል። ማንነት የማይገልፅ እና ሚስጥራዊ ነው።

የ MCPS ጠንካራ የተማሪ ፍላየሮች/በራሪ ወረቀቶች (በተለያዩ ቋንቋዎች)

English  /  español  /  中文  /  français /  Português /  한국어 /  tiếng Việt /  አማርኛ

ከባድ የማህበረሰብ ጤና ጉዳይ

ፈንታንየል/Fentanyl የመከላከል ትግል፡ እኛ እና አጋሮቻችን እንደተነጋገርንበት፤

ሕገወጥ የፈንትኒል አደገኛ አጠቃቀምን በተመለከተ ማኅበረሰባችን ምላሽ መስጠት አለበት። ጉዳዩን ለህብረተሰቡ ትኩረት እንዲሰጥ ያደረገው የመረጃ ስርጭት መድረኮች፣ የማህበረሰብ መልዕክቶች እና የካውንቲ ፖሊስ አጋሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና የወጣቶች አቀንቃኞች የተሳተፉበት ጉልህ የሚዲያ ዝግጅት ነው። ናርካንን ለትምህርት ቤቶቻችን ማስተዋወቅ ፌንታኒል ለመከላከል በምናደርገው ትግል ወሳኝ እርምጃ ነበር፣ይህም አዋቂዎች እና ተማሪዎች በድንገተኛ ጊዜ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል። እንዲሁም MCPS ጠንካራ የተማሪ የአእምሮ ጤና እና ደህንነት መተግበሪያ፣ የተማሪዎችን አእምሯዊ ደህንነት ለመደገፍ እና የአእምሮ ጤና ስጋቶችን ለመረዳት እንዲረዳቸው አስፈላጊ የአደጋ ጊዜ ግብአቶችን እና መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ የተነደፈ ጠቃሚ ሪሶርስ መኖሩን አስታውቀናል። ዶ/ር ፓትሪሺያ ካፑናን ይህን አሳሳቢ የማህበረሰብ ጉዳይ የመፍታትን አስፈላጊነት እንድናውቅ እና እንድናስተላልፍ ስለረዱን በዚህ አመት የት/ቤት ህክምና ኦፊሰር ቦታን ለማካተት ያደረግኩት ውሳኔ ተገቢ መሆኑን አረጋግጧል።


የካውንቲ መሪዎች፣ ህግ አስከባሪዎች እና አቀንቃኞች በተማሪ ኦፒዮይድ ከመጠን በላይ መውሰድ እና ሞት እየጨመረ መሄድ ጉዳይ አጽንኦት በመስጠት ተወያይተዋል

በትምህርት፣ በህግ አስከባሪ አካላት፣ በጤና አገልግሎት አደንዛዥ እጽ መከላከል ላይ ቁልፍ የሆኑ መሪዎች ጃንዋሪ 19 ተሰብስበው በህገ-ወጥ የኦፒዮይድ አጠቃቀም ላይ በተለይም በወጣቶቻችን ውስጥ ስለተስፋፋው ፌንታኒል የሚባለው ጎጂ ነገር አስደንጋጭ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል። መረጃው ከመጠን በላይ የመውሰድ ሁኔታን ብቻ ሳይሆን የሚያመለክተው የሞት መጠን መጨመሩንም ያሳያል። እነዚህን አደገኛ አዝማሚያዎች ለማህበረሰቡ ማሳወቅ ወሳኝ ነበር። ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ


ስለ ኦፒዮይድ እና ፈንታኒል/Opioid and Fentanyl የማህበረሰብ ውይይት መድረኮች 

የኦፒዮይድ መድሐኒት አጠቃቀም መስፋፋት የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ፣ ሞንትጎመሪ ጎስ ፐርፕል እና MCPS የመሣሰሉ አጋሮችን የማህበረሰብ ውይይት ለማድረግ መድረኮችን ፈጥሯል። ቤተሰቦች የአደንዛዥ እፅን መቅሰፍት ስለመዋጋት ታሪካቸውን አጋርተዋል። እነዚህ መድረኮች አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ሲሆኑ ከሁሉም በላይ፣ ቤተሰቦች ከሕገወጥ ኦፒዮይድ አጠቃቀምና ስርጭት ጋር በሚደረገው ትግል አጋሮች እና ደጋፊዎች እንዳላቸው እንዲገነዘቡ ረድተዋል።


MCPS ተማሪዎች ናርካን በትምህርት ቤት ናርካን መያዝ እንዲችሉ የሚፈቅደውን አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል

MCPS አንድ ግለሰብ ኦፕዮይድ ከመጠን በላይ መውሰዱ(ዷ)ን ሲጠረጠር በት/ቤት የድንገተኛ ህክምና እርዳታ መስጠት እንዲቻልአዲስ መመሪያ አውጥቷል። አዲሱ ደንብ ናሎክሶን/naloxone (በብራንድ ስሙ ናርካን (Narcan) በመባልም ይታወቃል) በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ውስጥ አጠቃቀሙን እና ተደራሽነቱን በተመለከተ ዝርዝር መመሪያን ያካትታል። ናርካን፡ ኦፒዮይድ ከመጠን በላይ በመጠጣት ምክንያት የሚያስከትለውን መጥፎ ጉዳት በጊዜያዊነት የሚቀይር ህይወትን ሊያድን የሚችል መድሃኒት ነው።

ክብረ በዓላት እና መልካም ዜና

የተማሪዎቻችንን፣ የሰራተኞቻችንን እና የማህበረሰብ አጋሮቻችንን አስደናቂ ስኬቶችን በተመለከተ አስደናቂ የምስራች ላካፍላችሁ በጣም ጓጉቻለሁ።


ምረቃዎች

ወደ 12,000 የሚጠጉ የኦንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የ 2023 ተመራቂዎች በምረቃ ሥነ ሥርአቶች ላይ ዲፕሎማ ተቀብለዋል። 

በዚህ አመት የምረቃ ስነስርአት ላይ መልእክት የሚያስተላልፉ ታዋቂ ተናጋሪዎች፡ የቶኒ ሽልማት አሸናፊ እና ተዋናይ የቀድሞው የቶማስ ኤስ. ዉተን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ማይለስ ፍሮስት (Myles Frost) በተማረበት ት/ቤት (alma mater; Maryland Lt.) ለተመራቂዎች ንግግር አድርገዋል። ገቨርነር አረና ሚለር (Gov Aruna Miller) በሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ንግግር አድርጓል፤ ባል እና ሚስት ጋዜጠኞች ፒተር ቤከር (Peter Baker) ከዊንስተን ቸርችል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተመረቁ ተማሪዎች ንግግር አድርገዋል። የኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪና ደራሲ እና የቴሌቪዥን አዘጋጅ ጆርጅ ፔሌካኖስ (George Pelecanos) ለተመራቂዎች ንግግር አድርገዋል። የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ እና የቀድሞ NBA ኮከብ ተጫዋች ዋልት ዊሊያምስ (Walt Williams) ለሼርዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች ንግግር አድርገዋል።


2023-2024 የትምህርት አመት የምግብ ዝርዝር ውስጥ ተማሪዎች የምግብ ጣእም ፈጠራ ጽንሰ ሃሳብን ለመረዳት ቅምሻ አድርገዋል

"Division of Food and Nutrition Services"/የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት ክፍል ሁለተኛውን ዓመታዊ "The Taste of MCPS" የምግብ ጣዕም ቅምሻ አስተናግዷል። የተማሪዎች አስተያየት 2023-2024 የትምህርት አመት የምግብ ዝርዝር ውስጥ ይካተታል።


(Milken Award) የፌርላንድ አንደኛ ደረጃ መምህር ብሔራዊ የማስተማር ሽልማት አግራሞት አግኝቷል

የፌርላንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲዮን ጆንስ/Dion Joneswas በታዋቂው Milken ብሔራዊ የማስተማር የክብር ሽልማት አግራሞት ተችሮታል። ይህ እውቅና ለትምህርት አርአያነት ያለውን ቁርጠኝነት እና የወጣት አእምሮን የማበረታታት ችሎታን ያጎላል።


የአመቱ ምርጥ የህፃናት መምህር ሻምፒዮናዎች

የህጻናት አገልግሎት ሻምፒዮን ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ። እነዚህ የተሰጧቸው ዕውቅናዎች ለትምህርት ያበረከቱትን የላቀ አስተዋጾ እና የተማሪዎቻቸውን አቅም ለመገንባትና ለመንከባከብ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያመለክታል። በክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልጅ እድገት መምህርት ሻነን ማኬንዚ/ Shannon McKenzie፣ 2023–2024 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህርት ሆናለች። ከዚህ ቀጥሎ ለሜሪላንድ የአመቱ ምርጥ መምህርነት ትወዳደራለች።


ሳሚ ሰኢድ/Sami Saeed ቀጣዩ ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል ሆኖ ተመርጧል

በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር ተማሪ ሳሚ/Sami 2023-2024 የትምህርት አመት ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል (SMOB) አባል ሆኖ ተመረጧል። የአቶ ሰኢድ የአገልግሎት ዘመን ጁላይ 1፣ 2023 ይጀምራል።


የላቀ አገልግሎት ሽልማቶች

ልዩ ትጋትን ያሳዩ እና ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ ጉልህ አስተዋፆ ያደረጉ ግለሰቦችን የላቀ አገልግሎት ሽልማታቸውን አክብሮት እንሰጣለን። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚያደርጉት ጥረታቸው እና የላቀ ቁርጠኝነታቸው በተማሪዎቻችን ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ጥርጥር የለውም።


አስራ ሰባት ተማሪዎች $2,500 ናሽናል ሜሪት ስኮላርሺፕ አኝተዋል

ከሰባት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ 17 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ናሽናል ሜሪት ስኮላርሺፕ ኮርፖሬሽን የሚደገፍ $2,500 ብሄራዊ ሽልማት ስኮላርሺፕ ተሰጥቷቸዋል። ተማሪዎቹ በሜሪላንድ ከሚገኙት 44 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች መካከል በቅርቡ ብሔራዊ የሜሪት ስኮላርሺፕ ፕሮግራም ካገኙት ውስጥ የተመረጡ ናቸው። ምሁራኑ የተመረጡት ከ15,000 በላይ የመጨረሻ እጩዎች መካከል ሲሆን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የአንድ ጊዜ የ2,500 ዶላር ሽልማት ያገኛሉ።


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ኢጁኬሽናል ፋውንዴሽን 194 "Rales-O’Neill $10,000 Scholarship" ስኮላርሺፕ ያገኙ ተመራቂዎችን አስታውቋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የትምህርት ፋውንዴሽን/MCPS Educational Foundation "2023 ሩት እና ኖርማን ራልስ ፓትሪሽያ ቤየር ኦ’ ኔል ስኮላርሽፕ/Ruth and Norman Rales-Patricia Baier O’Neill Scholarship" ያገኙትን 194 የላቀ ደረጃ አካዳሚክ ተሸላሚዎች ይፋ አድርጓል። በሞንትጎመሪ ካውንቲ በሁሉም 25 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ተመራቂዎች እነዚህ ከፍተኛ ስኮላርሺፖች እየተሰጡ ናቸው። ኮሌጅ በሚገቡበት ወቅት የሚደርስባቸውን የገንዘብ ጫና ለማቃለል ስኮላርሽፕ የተሰጣቸው እያንዳንዳቸው $10,000 ያገኛሉ።


አስራሶስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የተሟላ "Posse" ስኮላርሺፖችን አግኝተዋል

13 ተማሪዎች ከፖሴ ፋውንዴሽን "Posse Foundation" የአራት-ዓመት የኮሌጅ ትምህርት ሙሉ ስኮላርሺፕ አግኝተዋል። ይህም የሕዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመደበኛው የኮሌጅ ምርጫ ሂደት ችላ ሊባሉ የሚችሉ ልዩ አካዴሚያዊ እና የአመራር እምቅ ችሎታ ያላቸው ናቸው።


እነዚህን ድንቅ ግለሰቦች ስናከብር፣ እኛን የሚያበረታቱን እና ተማሪዎች የሚበለፅጉበት እና ለስኬት የሚበቁበት መንከባከቢያ አውድ ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያጠናክሩ አስደናቂ ስኬቶቻቸውን እናደንቃለን።

ለሠመር

ለሌላ የተሳካ የትምህርት ዘመን ስንሰነባበት፣ በሠመር ዕረፍት እና በመጪው የትምህርት አመት የሚጠብቀንን ደስታ እና እድሎች አሻግረን የምንመለከትበት ጊዜ ነው። ተማሪዎች እና ሰራተኞቻችን በብዙ የሰመር ትምህርት ፕሮግራሞች ይጠመዳሉ፣ተማሪ-አትሌቶች ለፎል የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ለመጀመር ይዘጋጃሉ፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ፣ ካቢን ብራንች አንደኛ ደረጃ ት/ቤት "Cabin Branch Elementary" የተሰኘ አዲስ ትምህርት ቤት በክላርክስበርግ/Clarksburg ለመክፈት እንዘጋጃለን።

በፀሀያማ ቀናት ድማስ ላይ፣ የሠመር ወቅት በልዩ ልዩ የሠመር እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ፣ አዳዲስ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችን ከመቃኘት ጀምሮ በተለያየ የጀብድ እንቅስቃሴዎች ጭምር ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ጥሩ ጊዜ እስከማሳለፍ ግንዛቤዎን የሚያሰፉበት ጊዜ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የእኛ ቆራጥ አስተማሪዎች እና አስተዳዳሪዎቻችን ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን በትጋት እየተዘጋጁ ናቸው። 

ሰኞ፥ ኦገስት 28 የሚጀመረውን የትምህርት ቀን በጉጉት እንጠባበቃለን፣ ወደ ሌላ አስደናቂ የመማር፣ የእድገት እና የስኬት ጉዞ ለመግባት ተዘጋጅተን በአንድነት የምንሰበሰብበት ጊዜ ይሆናል። ትምህርት ቤት በሚጀመርበት የመጀመሪያው ቀን በሠላም እንገናኝ!


መገልገያዎች/ሪሶርሶች

ሠመሩን በአዝናኝ እድሎች እና እንቅስቃሴዎች ለማሳለፍ የሚያግዙ አንዳንድ ግብዓቶችን እዚህ ያገኛሉ።

የተቸገሩ ተማሪዎችን ይደግፉ / "BaCKPacks" ዘመቻ ዛሬውኑ ይለግሱ



ወደ ት/ቤት የመመለስ አውደ ርእይ–"2023 Back-to-School Fair" ቀጠሮ ያዙ።

ቀኑን ቀጠሮ ያዙ፡ 2023-2024 ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርእይ ቅዳሜ፥ ኦገስት 26 ዳግም በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ አዳራሽ/ Westfield Wheaton mall ይካሄዳል። ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ትልቅ እና የተሻለ ይሆናል። ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ!