Skip to main content

Amharic 09-14-2023


ሴፕቴምበር 6, 2023

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች "Implement Remind" የተሠኘ አዲስ የግንኙነት መተግበሪያ

"Remind App" መተግበሪያ ምንድን ነው?

"Remind" በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች፣በመምህራን፣በተማሪዎች እና በወላጆች መካከል ለኝኙነት  የሚያገለግል የመልእክት ማስተላለፊያ ነው። የት/ቤት ሰራተኞች፣ የማእከላዊ ቢሮ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና ወላጆች የጽሁፍ መልእክት፣ ኢሜል ወይም የስልክ ጥሪ እና በመረጡት ቋንቋ ተመራጭ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም መልዕክቶችን እንዲልኩ እና/ወይም እንዲቀበሉ ለማስቻል ሁሉም "Remind" አካውንት ይኖራቸዋል።

 

የእኔ ትምህርት ቤት የሚጠቀምበት መቼ እና እንዴት ነው?
በዊንተር ዕረፍት፥ ትምህርት ቤቶች "Remind app" መተግበሪያን በመደበኛነት ወደመጠቀም  ይሸጋገራሉ። ትምህርት ቤትዎ ይህንን መተግበሪያ ለመጠቀም ሽግግር ሲያደርግ፣ ወላጆች እና ትልልቅ ተማሪዎች ከመምህር(ራን) የጽሁፍ መልእክት ወይም የኢሜይል ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

ለወላጆች

ወላጆች በኢንተርኔት ወይም "Remind app" መተግበሪያ በመጠቀም "Remind" አካውንታቸውን መክፈት/መግባት ይችላሉ።

ለተማሪዎች

ዕድሜያቸው 13 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከአስተማሪዎች ለሚደርሳቸው መልእክት ምላሽ መስጠት ይችላሉ። ሁሉም ተማሪዎች "Log in to Google option, which uses their MCPS Google apps credentials" የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ  (MCPS) ጉግል አፕሊኬሽኖቻቸውን በመጠቀም "Remind" አካውንታቸውን/መለያቸውን መክፈት/መግባት ይችላሉ። ዕድሜያቸው 13 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሞባይል ያላቸው ተማሪዎች "Remind app" መተግበሪያ አውርደው “Log in to Google” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም መግባት/መክፈት ይችላሉ።

 

ወደ ትምህርት ቤት የተመመለስ ዝግጅቶችን የሚያስተናግዱ ትምህርት ቤቶች

የዋትኪንስ ሚልስ ክላስተር ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 14 ቀን 6–8 p.m. የመጀመሪያውን "ወደ ት/ቤት የመመለስ ብሎክ ፓርቲ" በጋራ ያስተናግዳል። ይህም ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት ከሴፕቴምበር ወር ጀምሮ እየተከናወኑ ካሉት ዝግጅቶች አንዱ ብቻ ነው። ዝግጅቱ የሚካሄድበት አድራሻ፦ Montgomery Village Middle School, 19300 Watkins Mill Road in Montgomery Village

 

ስለ ትምህርት ቤትዎ የዚህ አመት ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ምሽት ቀን እና ሰዓት ከተማሪዎ ትምህርት ቤት ጋር መነጋገርዎን ያረጋግጡ።

 

ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የስቴት ምዘና/ፈተና በተመለከተ ጠቃሚ መልክት

ከዚህ የትምህርት አመት ጀምሮ ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች (2027 ክፍል)፣ ለባዮሎጂ እና ስነመንግስት ኮርስ የሜሪላንድ አጠቃላይ ምዘና/ፈተና  በእያንዳንዱ ኮርስ ከተማሪው የመጨረሻ ክፍል 20 በመቶ ተሰልቶ ይመዘገብላቸዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማጋራት ቨርቹዋል የወላጆች ምሽት በዚህ ፎል ይዘጋጃል።

የሂስፓኒክ ቅርስ የሚከበርበት ወር

የሂስፓኒክ ቅርስ የሚከበርበት ወር ከሴፕቴምበር 15 እስከ ኦክቶበር 15 ነው። በወሩ ውስጥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች የዘር ሀረጋቸው ከስፔይን የሆነ እና ከሌሎች ስፓኒሽኛ ተናጋሪ ሀገራት በሰሜን አሜሪካ፣መካከለኛው አሜሪካ፣ ከደቡብ አሜሪካ እና ከካሪቢያን የመጡ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ሰራተኞችን እና የማህበረሰብ አባላትን ልዩ ባህል እና ወግ ያከብራሉ።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ውስጥ ስፓኒሾች እና ላቲኖዎች 34 በመቶው የተማሪዎች ቁጥር በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኙ ብሄረሰቦች ናቸው። የሒስፓኒክ ቅርስ መታሰቢያ ወርን ስለማክበር MCPS ሪሶርሶች እዚህ ይገኛሉ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሠራተኞች ሁሉ ከእኛ ጋር እንዲያከብሩ እንፈልጋለን! ቅርሳቅርሶችን የሚወክሉ ምስሎችን ያጋሩን እና MCPS በቨርቹዋል የመረጃ ቋት/ጋለሪ ላይ ያቀርበዋል። ምስሎችን/ፎተግራፎችን በዚህ አድራሻ ኢሜይል ያድርጉ pio@mcpsmd.org።

ቦርዱ በሶስት ፖሊሲዎች ላይ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ይፈልጋል

የትምህርት ቦርድ በሶስት ፖሊሲዎች ላይ በቀረቡት የማሻሻያ ሃሳቦች ላይ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል፦

ፖሊሲ ABC፣ የወላጅ እና የቤተሰብ ተሳትፎ

ፖሊሲ BLB፣ በይግባኝ እና የችሎት ሂደት ውስጥ ያሉ የአሰራር ህጎች

ፖሊሲ IJA፣ በትምህርት ቤቶች የካውንስሊንግ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች

የቋንቋ ትርጉሞች ይገኛሉ።

  • ፖሊሲ ABC ረቂቅ ማሻሻያዎች ላይ ከፌብሩዋሪ 9, 2023 ጀምሮ አስተያየት ለመስጠት የሚቻል ሲሆን ሴፕቴምበር 18 የአስተያየት መስጫው ጊዜ ያበቃል። የቦርዱ ፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ኦክቶበር 10, 2023 በሚያደርገው ስብሰባ የህዝብ አስተያየቶችን ለመገምገም የጊዜ ቀጠሮ ተይዟል።
  • የፖሊሲ BLB ረቂቅ ማሻሻያዎች ከጁላይ 7, 2023 ጀምሮ አስተያየት ንዲሰጥበት የቀረበ ሲሆን የአስተያየት መስጫው ጊዜ ሴፕቴምበር 18 ያበቃል። የቦርዱ ፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ኦክቶበር 10, 2023 በሚያደርገው ስብሰባ የህዝብ አስተያየቶችን ለመገምገም የጊዜ ቀጠሮ ተይዟል።

  • የፖሊሲ IJA ረቂቅ ማሻሻያዎች ከአፕሪል 26, 2023 ጀምሮ ለአስተያየት ቀርቧል፣ እና የአስተያየት መስጫው ጊዜ ኖቬምበር 6, 2023 ይዘጋል። የቦርዱ የፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ዲሴምበር 14, 2023 በሚያደርገው ስብሰባ የሕዝብ አስተያየቶችን ለመገምገም የጊዜ ቀጠሮ ተይዞለታል።

የተደረጉት ለውጦች፣ የለውጦቹ ረቂቅ እና የህዝብ አስተያየት መጠይቆች መግለጫ የህዝብ አስተያየት መስጫ ገጽ ላይ ይገኛሉ።

የፎል የወላጅ አካዳሚ መርሃ ግብር የጊዜ ሠሌዳ አሁን ይገኛል

ቤተሰቦች እና ተማሪዎች በትምህርት ዓመቱ በሙሉ ከፓረንት አካዳሚ-Parent Academy TO GOጋር ተጎዳኝተው መቆየት አለባቸው። ፓረንት አካዳሚ-Parent Academy TO GO ማለት ቤተሰብ እቤታቸው እንዲመለከቱ በቪድኦ የሚቀርብ ቨርቹወል ውይይት ነው።

የሴፕቴምበር፣ የኦክቶበር፣ የኖቬምበር እና የዲሴምበር ዌብናሮች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፥ እንዲሁም የወላጅ አካዳሚ ድረገጽ ላይ ይገኛሉ። ለመመዝገብ እዚህ ይክፈቱ።

 

ሴፕቴምበር

የመማሪያ መንገዶች፦ ልጅዎን በቤት ይደግፉ

ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 11

6-7 p.m.

የመድረሻ ኮሌጅ፦ የኮሌጅ መግቢያ ሂደትን መረዳት

ረቡዕ፣ ሴፕቴምበር 13

6-7 p.m.

አዲስ የትምህርት ዓመት፣ አዳዲስ ስልቶች፡ በዚህ አመት እንዴት ማቀድ፣ በጽናት መሻገር እና የአካዳሚክ ስኬት ማግኘት እንደሚቻል

ረቡዕ፣ ሴፕቴምበር 27

6-7 p.m.

ከማፈግፈግ ወደ ተግባር

ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 28

6-7 p.m.

ኦክቶበር

የቤት አካባቢን አረንጓዴ የማድረግ ስልቶች

ሰኞ፣ ኦክቶበር 2

6-7 p.m.

MCPS አትሌቲክስ – #WeR.A.I.S.E.

ሐሙስ፣ አክቶበር 5

6-7 p.m.

አወንታዊ ዲሲፕሊን

ረቡዕ፣ ኦክቶበር 11

6-7 p.m.

ተግባራዊ ወላጅነት አሁን!

ሐሙስ፣ አክቶበር 12

6:30-8:30 p.m.

ይህ ከአራት ተከታታይ ክፍሎች የመጀመሪያው ክፍል ነው። በአራቱም ወርክሾፖች ላይ እንዲገኙ እናበረታታለን።

 

ጥንቁቅነት፦ በከባድና አስቸጋሪ ጊዜዎች ውጥረትን/ጭንቀትን መቆጣጠር

ሰኞ፥ ኦክቶበር 16

6:30-7:30 p.m.

በቤት ውስጥ የስነ ልሳን ችሎታዎችን መገንባት

ማክሰኞ፥ ኦክቶበር 17

6-7 p.m.

ለህጻናት እና ለታዳጊዎች ኦንላይን የደህንነት ምክሮች

ረቡዕ፥ ኦክቶበር 18

6-7 p.m.

ተግባራዊ ወላጅነት አሁን!

ሐሙስ፣ አክቶበር 19

6:30-8:30 p.m.

ይህ ከአራት-ተከታታይ ክፍሎች ውስጥ ሁለተኛው ክፍል ነው። በአራቱም ወርክሾፖች ላይ እንዲገኙ እናበረታታለን።

የኮሌጅ ፍኖተ ካርታ፦ ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎልተው እንዲወጡ ምን ማድረግ አለባቸው

ረቡዕ፥ ኦክቶበር 25

6-7 p.m.

ተግባራዊ ወላጅነት አሁን!

ሐሙስ፣ አክቶበር 26

6:30-8:30 p.m.

ይህ ከአራት ተከታታይ ክፍሎች ውስጥ ሶስተኛው ክፍል ነው። በአራቱም ወርክሾፖች ላይ እንዲገኙ እናበረታታለን።

ኖቨምበር

አዲሱ ዲጂታል SAT፡ ማወቅ ያለብዎት ሁሉም ነገር

ሐሙስ፣ ኖቨምበር 2

6-7 p.m.

ተግባራዊ ወላጅነት አሁን!

እሮብ፥ ኖቨምበር 8

6:30-8:30 p.m.

ይህ ከአራት ተከታታይ ክፍሎች ውስጥ አራተኛው ክፍል ነው። በአራቱም ወርክሾፖች ላይ እንዲገኙ እናበረታታለን።

በቤት ውስጥ የስነ ልሳን ችሎታዎችን መገንባት

ማክሰኞ፥ ኖቬምበር 14

6-7 p.m.

በታዳጊ ወጣቶች የፍቅር ግንኙነት ጥቃትን ለመከላከል የወላጅ መመሪያ

ሐሙስ፣ ኖቨምበር 16

6-7 p.m.

ዲሴምበር

ስለ ፈንታንይል (Fentanyl) ጎጂነት እውነታዎች

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 14

6-7 p.m.

ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተደረገ ጥሪ፡ MoCo EmpowHER ለፎል የአመራር ተቋም አሁኑኑ አመልክቱ

 

የአመራር እና የማስተማር ችሎታን ለማዳበር ፍላጎት ያለህ(ሽ) የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ነህ(ሽ)? MoCo EmpowHER የፎል አመራር ተቋምን ይቀላቀሉ!

 

MoCo EmpowHER ተልእኮ በወሲባዊ ጥቃት፣ በፆታዊ ግንኙነት እና በፆታ ላይ ስለተመሰረተ መድልዎ ለመወያየት አስተማማኝ ሁኔታ ለመፍጠር በካውንቲው ውስጥ ጠንካራ የሴቶች ማህበረሰብን ማፍራት ነው። በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተሳታፊዎች በአደባባይ በህዝብ ፊት ንግግር ማድረግን፣ በቡድን ግንኙነት እና በአደረጃጀት ላይ በሚሰጡ ትምህርቶች የአመራር ክህሎትን በማዳበር ላይ ያተኮሩ ቨርቹዋል እና በአካል በሚሰጡ የሳምንታዊ አውደ ጥናቶች ላይ ይሳተፋሉ። ስውር አድሎአዊነት፣ በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚታየው የፆታ የበላይነት ስሜት እና የፆታ እኩልነት እና የሴቶች መብት ጉዳዮች የመሣሰሉ ትምህርቶችም ይሰጣሉ።

 

ተሳታፊዎች በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ በአካል ተገኝተው እኛ ባስታጠቅናቸው/ባቀዳጀናቸው መገልገያዎች የሠሩትን እና ያከናወኑትን ውጤት ለማክበር አብረውን የመገኘት ዕድል እንዳላቸው ሳንጠቅስ አናልፍም። ወደ አመራር ተቋሙ ለማመልከት ይህን አገናኝ/ሊንክ ይጠቀሙ። ማመልከቻ የሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ሴፕቴምበር 22 ቀን 11፡59 p.m. ነው።

 

የግሌንስቶን ሙዚየም ነፃ የትምህርት ቤት ጉብኝቶችን ያስተናግዳል፣ እስከ ጃንዋሪ 2024 ድረስ በኦንላይን ቦታ ይያዙ

ለ2023–2024 የትምህርት አመት፣ የግሌንስቶን ሙዚየም መርሐግብርን በቦታው ላይ፣ የሚስተናገድ ጉብኝት ለአስተማሪዎች የበለጠ እንከን የለሽ የሚያደርግ አዲስ የቦታ ማስያዣ የምዝገባ ገጽ ጀምሯል። ይህ አዲስ ሲስተም ሴፕቴምበር 1 እና ጃንዋሪ 26, 2024 መካከል የሚስተናገዱ ጉብኝቶችን የጊዜ ሰሌዳ ለማስያዝ በሥፍራው መገኘት ያስፈልጋል።

የፖቶማክ ሙዚየም ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ከሥነ ጥበብ፣ ከሥነ ሕንፃ እና ከተፈጥሮ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነትን በሚያሣልጥ አካባቢ የመማር እድሎችን ይሰጣል።

ግሌንስቶን (Glenstone) በቦታው ላይ የሚስተናገዱ ጉብኝቶችን እና ቨርቹዋል የተሳትፎ አማራጮችን መስጠት ይቀጥላል። የት/ቤታችን መርሃ ግብር ለብዙ የስርዓተ ትምህርት እና የክፍል ደረጃዎች የታለመ ሲሆን ቀጥተኛ ተሳትፎን ለማበረታታት የእርስበርስ ግንኙነት ልምምዶችን ይጠቀማል።

ከጊዜያዊ ኤግዚቢሽን ጋር በጥምረት Ellsworth Kelly at 100 በትምህርት ቤታችን ጉብኝቶች ኬሊ (Kelly) በዘመናዊ የስነጥበብ አለም ያበረከተቻቸውን ጠቃሚ አስተዋፆዎች በማካተት በልጽጓል። ስለትምህርት ቤታችን ፕሮግራም የበለጠ ለማወቅ፣ ድረ ገጹን ይጎብኙ

ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ግሌንስቶን (Glenstone) ነፃ የአውቶቡስ ማጓጓዣ እና ለሁሉም ጉብኝቶች የምትክ መምህራን ሽፋን ይሰጣል። ጉብኝት ከተደረገ በኋላ ተጨማሪ ዝርዝሮች ይሰጣሉ።

በጣቢያው ላይ የሚካሄድ ጉብኝት ለመጠየቅ፣ እዚህ ጠቅ ያድርጉ። ቨርቹዋል ተሳትፎ ለመጠየቅ፣ እዚህ ጠቅ ያድርጉ

ግሌንስቶን - Glenstone የሚገኝበት አድራሻ፦ 12100 Glen Road in Potomac

መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦

ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 7 – የትምህርት ቦርድ ስብሰባ

ቅዳሜ፥ ሴፕቴምበር 9 – ACT ፈተና ይሰጣል