Skip to main content

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፍትሃዊነት-የሚዛናዊነት ጉዞ

ሁሉም ማለት ሁሉንም የሚያካትት በመሆኑ
ተደራሽነት እና እድሎች ለሁሉም ተማሪዎች እንዲሆን መሥራት አስፈላጊ ሲሆን

በማስተማር፣ በአመራር፣ እና በመማር ረገድ ዘር፣ ጎሣ፣ እና ባህል ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። ለበርካታ ዓመታት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለተማሪዎች ጥብቅ፣ ትርጉም ያለው ትምህርት ለመስጠት ሲሠራ የቆየ ነው፣ ነገር ግን ሁሉ ተማሪዎች ከፍተኛ ደረጃዎች ላይ እየደረሱ አለመሆኑን መረጃዎች ያረጋግጣሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በግልጽነት እና በድፍረት የሚጠይቀው፣ ህዝባዊ ትምህርት ሁሉንም ተማሪዎች በእኩልነት እና በፍትሃዊነት ማገልገል እንደሚገባ የሚያምን ሲሆን ይህም የፍትሃዊነትና የሚዛናዊነት ጉዞ እምነቱ ለዲስትሪክት አቀፍ እሴቶች፣ ለስትራቴጂያዊ እቅድ እና የበጀት ዝግጅት ማዕከል ነው። የዛሬው "ሁሉም ነገር፦ የእኩልነትና ውጤታማነት ማዕቀፍ" የሚያርፈው ለዓመታት በእውቀት ላይ በተመሰረተ፣ ጠንክሮ በመስራት መሠረት ላይ ነው ። የዚህ ስራ አስፈላጊ ማጣቀሻዎች-ማመሣከሪያዎች በዚህ ድረገጽ ላይ ቀርበዋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፍትሃዊነት-የሚዛናዊነት ጉዞ

የጊዜ ማእቀፍ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፍትሃዊነት-ሚዛናዊነት ምሳሌዎች

All Means All/ሁሉም ማለት ሁሉንም ነው

የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተልእኮ ሁሉም ተማሪ በኮሌጅ ፣ በሥራ፣ እና በማህበረሰቡ ዘንድ በወገንተኝነት ያልሆነ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችሉት/የሚያስችላት የአካደሚክ፣ ፕሮብሌሞችን/ችግሮችን የመፍታት የፈጠራ ችሎታ፣ እና ማህበራዊ እና ስሜታዊ ክህሎቶች እንዲኖሩት/እንዲኖሯት ማረጋገጥ ነው። በርካታ ተማሪዎቻችን በከፍተኛ ደረጃ ስኬታማነትን እየተጎናጸፉ ቢሆንም፣ ብዙዎች ግን ይሄን አድልና ድጋፍ እንዲሁም ያላቸውን እምቅ አቅም በቁምነገር ለመጠቀም የሚያስችላቸው መገልገያ ግብአቶችን አግኝተው አያገኙም፣ በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ፣ እና በሁሉም ት/ቤቶቻችን፣ ለሁሉም ተማሪዎች በእድል እና በስኬት ረገድ ያለውን ክፍተቶች በመዝጋት በተማሪ ውጤቶች ላይ ያለዉን ልዩነቶች/የአለመመጣጠን ለመፍታት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በቁርጠኝነት ይሰራል። (በሁሉም ቋንቋዎች ይገኛል።)

ሁሉንም ማቀፍ፦ ፍትሃዊነት እና የስኬት ማዕቀፍ

የመማር ማረጋገጫ

1

የተማሪን የትምህርት እድገት መለካትየተማሪን የትምህርት እድገት መለካት
የመማር ማረጋገጫ (EOL)

የተማሪን መማር በመማሪያ ክፍል ዉስጥ፣ በዲስትሪክት እና በውጭ ፈርጆች/ዘርፎች የሚገመግሙ/የሚዳስሱ በርካታ እርምጃዎች

2

ስለ ለተማሪ ስኬታማነት ማቀድ (icon) ስለ ለተማሪ ስኬታማነት ማቀድ
ትምህርት ቤትን የማሻሻል እቅድ አሠራር-ሒደት (SIP)

በርካታ መመዘኛ መስፈርቶችን የማያሟሉ ተማሪዎችን ለመለየት መረጃ/ዳታ የመጠቀም ስልት እና ያሟሉትን ደግሞ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የማሻሻያ ናሙና/ሞዴል

3

ትምህርት ቤት ያለበትን ሁኔታ-የሚያሳድረውን ተጽእኖ መገምገም (icon) ትምህርት ቤት ያለበትን ሁኔታ-የሚያሳድረውን ተጽእኖ መገምገም
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፕበሊክ ስኩልስ (MCPS) የሚዛናዊነት-የፍትሃዊነት ሃላፊነትና ተጠያቂነት ሞዴል

በርካታ መመዘኛ መስፈርቶችን የማያሟሉ ተማሪዎችን ለመለየት መረጃ/ዳታ የመጠቀም ስልት እና ያሟሉትን ደግሞ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የማሻሻያ ናሙና/ሞዴል

የመማር ማረጋገጫ

የፍትሃዊነት ተጠያቂነት/ሀላፊነት አርአያ/ሞዴል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፍትሃዊነትና የሚዛናዊነት ሃላፊነትና ተጠያቂነት ሞዴል* ስለትምህርት ቤቶች ስኬታማነት ዝርዝር ዳሰሳ የሚያደርግ ሲሆን የሁሉንም ተማሪዎች ክንውን በይፋ ሪፖርት ይሰጣል። የ ተገቢነት፣ ትክክለኛነት፣ ሚዛናዊነት-ተጠያቂነት/ሀላፊነት አርአያ አይነት ከተለመደው አይነት የስቴት እና የፌደራል ጅምላ የሪፖርት አቀራረብ ባለፈ መልኩ/ባሻገር ተመሣሣይ/እኩል ተደራሽ እድል ወይም እንደሌሎች ስኬታማ የመሆን እድል ባላገኙት የተማሪዎች ትኩረት ቡድን ላይ በዝርዝር ሪፖርት የማድረግ ሥራ ይሠራል።

እንዴት እናውቃለን? ካልሆነስ፣ ለምን አልሆነም?

የፍትሃዊነት ተጠያቂነት/ሀላፊነት አርአያ/ሞዴል

ሚዛናዊ-ፍትሃዊ የሪሶርሶ ተደራሽነት

ትምህርት ቤቶች ሠራተኞችን፣ ጊዜን እና ገንዘብን በተማሪ ውጤታማነት የስኬት ማእቀፍ ሚዛን ሲታይ በአምስቱ የትኩረት ቡድኖች ክንዋኔ አንፃር ፍትሃዊ የሪሶርሶች ተደራሽነትን (EAR) ሲስተሙ እንዴት በትክክለኛ ሚዛናዊነት እየተጠቀመ እንደሆነ በከፊል ይመረምራል። በሲስተሙ የሚገኙ ሪሶርሶች ምደባ እና አጠቃቀምን በጥልቀት ግምገማ የማድረግ ዋናው ግብ አስቀድሞውኑ የተተለመ በዘር ወይም በገቢ መጠን ላይ የሚመሠረት ሚዛን ያልጠበቀ የተማሪ ስኬታማነትን ለመቀነስ ነው።

ስለዚህ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ሚዛናዊ-ፍትሃዊ የሪሶርሶ ተደራሽነት

በሚድያ ላይ

አስተያየት ማቅረቢያዎች-መለጠፊያዎች

ዋሽንግተን ፖስት
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች ውስጥ እያደገ ያለው የውጤታመነት ልዩነት ክፍተት መስተካከል አለበት
ሃሳቡን ያቀረቡት Jack R. Smith

ሜይ 3/2019 በ 9:00 a.m. EDT


በሞንቶጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ብዙ የካውንቲአችን ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ከፍተኛ አድናቆት የሚገባቸው እና ሽልማቶችንም ያገኙ ቢሆንም ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ግን በአንፃሩ የስኬት ልዩነት ክፍተቱ እያደገ ሄዷል። የካውንቲው መሪዎች ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ክፍተቱ ተባብሶ ቀጥሎአል፣ በተወዛጋቢ መረጃ ተዳፍኖ አንዳንድ ተማሪዎች በትልቅነቱ አንደኛ በሆነው የአገሪቱ የትምህርት ቤት ዲስትሪክት ውስጥ በእኩዮቻቸው ውጤት ሳቢያ እንዲደበዝዙ አስችሏል

ይበልጥ ያንብቡ


Bethesda Beat
አስተያየት፦ ሁሉም ተማሪዎቻችን ከፍ ያለ ግምት እንደሚሰጣቸውና አቅማቸው በፈቀደ መጠን እንደሚማሩ ሆኖ እንዲሰማቸው "የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንተንደንት የዘረኝነት ድርጊትን በማስወገድ ዓላማ አጣዳፊና አስቸኳይ ጥሪ ያደርጋል
በ ጃክ ስሚዝ/Jack Smith

ህትመት፦ 2020-07-11 00:49


አብዛኛዎቹን አመታት፥ የጁላይ አራትን በዓል ከቤተሰቤና ከጓደኞቼ ጋር በማሳልፍበት ጊዜ፣ ርችት በሚታይበት ወቅት በልጄ ልጅ ፊት ላይ የሚታየውን ደስታ በመመልከትና ባሳለፍኳቸው ጁላይ 4 ክብረበዓላት የት እንዳለሁ በማሰላሰል በርካታ በዓላትን አልፌአለሁ።

ይበልጥ ያንብቡ


ጦማር

ስለ ሚዛናዊነት-ፍትሃዊነት ጉዳዮች የሚገልጽ የሱፐርኢንተንደት ስሚዝ (Smith's) ጦማር

ሁሉንም በአንድነት፦ የፍትህ እና የሚዛናዊነት ጥሪ

ሜይ 31/2020


የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፈተናዎችን እየተጋፈጥን ስንሄድ፣ እንዴት ሁላችን በአንድነት እንደምንሆን "በዚህ ሁላችን አብረን ነን-all in this together" በሚል ርዕስ ለብዙ ሳምንታት እየጻፍኩ ነበር። ይሁን እንጂ አሁን መግለጽ ያለብኝ መፍትሔ ማግኘት ያለበት ሌላም ችግር በአገራችን አለ። ይኼውም ሁላችንም የሚያጋጥመን የፍትሕና የእኩልነት ችግር ነው፤ ሁላችንም አንድ ላይ ሆነን ሳለ፣ ይህን ቀውስ ግን ሁላችን በአንድ መልክ እያጋጠመን አይደለም - ሌላው ቀርቶ ተቀራራቢነት እንኳ የለውም።

ይበልጥ ያንብቡ


ሁላችን በአንድነት፡- በጥላቻ ፣ በአድልዎና በመድልዎ ላይ በግልጽ አውጥተን መናገር/መነጋገር አለብን

ጃኑወሪ 20/2021


ማንም ሰው በቆዳው ቀለም ወይም በማንነቱ ወይም በሃይማኖቱ ምክንያት ሌላውን ሰው ጠልቶ አይወለድም። ሰዎች ጥላቻን ይማራሉ፤ ጥላቻን መማር ከቻሉ ደግሞ ፍቅርንም መማር ይችላሉ፤ ምክንያቱም ፍቅር ከተቃራኒው (ከጥላቻ) ይልቅ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ በሰዎች ልብ ውስጥ ይሰፋል። - Nelson Mandela/ኔልሰን ማንዴላ

ተማሪዎች ከፍ ያለ የትምህርት ደረጃ ላይ ለመድረስ የደስታ ስሜት ሊሰማቸው ያስፈልጋል። አካላዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል። ማንነታቸው የሚከበርላቸው ምህዳር ያስፈልጋቸዋል ከጥላቻና ከአድልዎ ነፃ የሆኑ ትምህርት ቤቶችና ማኅበረሰብ ይፈልጋሉ።

ይበልጥ ያንብቡ


ስለሚዛናዊነትና ፍትሃዊነት ገጽታ በአብዛኛው የሱፐርኢንተንደንቱ ጦማር ላይ ሲገለጽ ቆይቷል፦


ሁሉ በአንድ ላይ፦ ተማሪዎቻችንን ለወደፊት ስኬት ለማዘጋጀት የሚደረግ ኢንቨስትመንት

ዲሴምበር 19/2019


አብዛኛውን ጊዜ ስናገር የነበረው ስለ እያንዳንዱ ተማሪ ለኮሌጅ ወይም ለሙያ የሚያዘጋጅ ትምህርት እንደሚያገኝ-እንደምታገኝ ለማረጋገጥ ስላለብን የሞራል ግዴታን በሚመለከት ነበር።

ይበልጥ ያንብቡ


ሁሉም አንድ፦ ገንዘባችንን እንዴት/የት እንደምናጠፋ ወሳኝነት አለው

ዲሴምበር 4/2019


ፎል መገባደጃ ለእኛ የትምህርት ቤት ሲስተም የባጀት ወቅት ነው። ስለ ባጀት ላይ ላዩን ሲታሰብ፥ ደረቅና አሰልቺ ቢመስልም ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች እንድንገመግምና ገንዘባችንን ትኩረት መስጠት ባለብን ነገር ላይ እንድናስቀምጥ ያስችለናል።

ይበልጥ ያንብቡ


ከትምህርት ቦርድ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ መግለጫ፦ ስለ እኩልነት፣ ሚዛናዊነት፣ ፍትሃዊነት እና ምጡቅነት ቁርጠኝነት

ሜይ 30/2020


ልጆች እና ማህበረሰቡ በቅርቡ ስለተከሰተው የጆርጅ ፍሎይድ (George Floyd) እና በረና ቴይለር (Breonna Taylor) አሰቃቂ ግድያ ሲያነቡ፣ ሲያዳምጡ እና ሲመለከቱ በይፋ አውጥተን መናገር የእኛ አጣዳፊና አስቸኳይ የሞራል ግዴታ ይሆናል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በሚናፖሊስ (Minneapolis) የተፈጸመውን የሚ/ር ፍሎይድ (Mr. Floyd) አሰቃቂ ግድያ እና በሉይስቪል (Louisville) የሚ/ስ ቴይለርን አስከፊ ግድያ ያወግዛል። በተለይ በእነርሱ ላይ ዘግናኝ ግድያ የተፈጸመው በህግ አስከባሪ አማካይነት መሆኑ ተቀባይነት የሌለው ነው። እነዚህ ድርጊቶች ሕዝባችን ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ባሠቃዩት የረዥም ጊዜ ታሪካዊ ኢፍትሐዊ ድርጊቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።

ይበልጥ ያንብቡ


በኣድማስ ላይ

ዲስትሪክት አቀፍ ፀረ-ዘረኝነት አመለካከት፣ ግምገማ/ኦዲት

ፕሮጀክቱ ገና ሲጀመር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) በስድስት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ኦዲት የሚያደርግ የውጭ ተቋራጭ እንዲሳተፍ ያደርጋል፦

በተጨማሪ ይወቁ

የሥራ ግብረኃይል ብዝሃነት ስብጥር
የሥራ ሁኔታዎችና የእድገት ማነቆዎች
ስለ ሚዛናዊነት-ፍትሃዊነት K-12 የስርዓተ ትምህርት ግምገማ
የእኩል ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ የአሰራር ሂደት
የማኅበረሰብ ግንኙነትና ተሳትፎ
የትምህርት ቤቶች ባሕል ግምገማ

ቪዲዮች

የፍትሃዊነት ተጠያቂነት/ሀላፊነት አርአያ/ሞዴል
አጭር መግለጫ

የመማር ማረጋገጫ
አጭር መግለጫ

የፍትሃዊነት ተጠያቂነት/ሀላፊነት አርአያ/ሞዴል -
የምረቃ መጠን

የፍትሃዊነት ተጠያቂነት/ሀላፊነት አርአያ/ሞዴል -
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተማሪዎች

የፍትሃዊነት ተጠያቂነት/ሀላፊነት አርአያ/ሞዴል -
የአካል ስንክልና ያለባቸው ተማሪዎች

ስለ ትምህርታዊ ሚዛናዊነት እና ፍትሃዊነት እንዲሁም ምጡቅነት የጥቁር እና የጠይም መድረክ - የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ነጸብራቅ

የጥቁር እና የጠይም መድረክ -
ሙሉ የስብሰባው ቪዲዮ

በ MCPS ተዛማጅ ድረገጾች ወይም ፕሮግራሞች

የእኩልነትና ሚዛናዊነት ተነሳሽነት ዩኒት

ዘርና ባሕል በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ፖሊሲዎች፣ ልማዶችና መስተጋብሮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ከመሆናቸውም በላይ በዘር መድልዎ ላይ የተመሠረተ የስኬታማነት እና የውጤት ትንበያን ሊያስከትል ይችላል።

  • ይህ የዘር መድልዎ እያንዳንዱ ግለሰብ ስለሚያምንበትና ስለሚያደርገው ብቻ ሳይሆን ተቋማዊም ነው፡፡
  • ይህንን በዘር ላይ የተመሠረተ ትንበያን ተቋማዊ እንቅፋቶችን ለማስወገድ የባህላዊ ብቃት ፖሊሲዎችን፣ ልማዶችን እና ስነምግባሮችን ማሳየትና ማረጋገጥ አለብን።

በተጨማሪ ይወቁ

የሚዛናዊነትና እኩልነት ዩኒት

የጥናት ክበቦች ፕሮግራም

የጥናት ክበቦች ፕሮግራም፣ ቡድኖች ተፈታታኝ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ለማድረግ የሚያስችሏቸውን ግንኙነቶች፣ ግንዛቤዎችና ችሎታዎች እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።

የውይይቱ ሂደት ተሳታፊዎቹ የሚከተሉትን ነጥቦች እንዲያስተውሉ ይረዳቸዋል፦

  • የዘርና የባህል ልዩነቶችን በማቻቻልና ራስን በሌሎች ቦታ በማስቀመጥ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ይገነባል/ያዳብራል
  • የተለያዩ የዘር እና የባህል ልምዶች እና አመለካከቶችን የማዳመጥ እና የመወያየት ክህሎቶችን ያዳብራል
  • ለዘረኝነትና ለባሕል ልዩነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ እምነቶችን፣ ልማዶችንና ፖሊሲዎችን ለመለየት የሚያስችል ማዕቀፍ ይጠቀሙ
  • ለትምህርት ቤት፣ ለቢሮ ወይም ለማኅበረሰቡ ሚዛናዊነት እና እኩልነትን በተመለከተ ምን እንደሚመስል የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያደርግ ራዕይ አዘጋጅ።

በተጨማሪ ይወቁ

በጀርባዋ ባክባግ (ቦርሳ) የያዘች ልጅ

ፍትሃዊ የተሃድሶ ተነሣሽነት

ፍትሃዊ ተሃድሶ ማለት ማህበረሰብን፣ ራስን መንከባከብን፣ እና የግጭት አፈታትን የመገንባት አቀራረብ ነው። ይኼውም ለተማሪዎች የሚጠቅም የማህበራዊ ፍትህ መድረክ ነው፦

  • ራሳቸውንና ኅብረተሰቡን የሚነኩ አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ማኅበራዊና የዲሲፒሊን ጉዳዮችን በንቃት በመከታተል መፍትሔ ጭምር ይሻሉ።
  • ለሚያደርጓቸው ነገሮች ኃላፊነት መውሰድ።
  • በዚህ ድርጊት ጉዳት የደረሰባቸውን አባላት እና የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደነበሩበት ለመመለስ እና / ለመጠገን ከተጎዱት ጋር ይሰራል።

በተጨማሪ ይወቁ

የፍትህ አርማ