Skip to main content

Other Languages: English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

የትምህርት ቦርድ ለዲስትሪክት 3 ክፍት የሥራ ቦታ አመልካቾችን ይፈልጋል

boe logo ROCKVILLE, MD— ሴፕቴምበር ላይ ወይዘሮ ፓትሪሺያ ኦኔል በመሞታቸው ምክንያት የተፈጠረውን ክፍት ቦታ ለመሙላት በሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ዲስትሪክት 3 የሚኖሩ ግለሰቦች ለመወዳደር እንዲያመለክቱ ተጋብዘዋል።
የዚህን ዓመት ቀሪ ጊዜ ለማጠናቀቅ የግለሰብ ምደባ በትምህርት ቦርድ ይከናወናል። የምደባው ሂደት የቀረቡ ማመልከቻዎችን መገምገም፣ የተናጠል ቃለ-መጠይቆች፣ የመራጭነት ምዝገባ ማረጋገጫ እና የድስትሪክት ነዋሪነት ማረጋገጥን ያካትታል። ቦርዱ የተመረጡትን እጩዎች ኖቬምበር 30/2021 ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እና ከዚያ በኋላ ብዙ ሳይቆይ የምደባውን ሂደት ለማጠናቀቅ ይፈልጋል።

በሕጉ መሠረት፣ የተመረጠ/ችው ግለሰብ በሞንጎመሪ ካውንቲ የተመዘገበ/ች መራጭ እና የተወሰኑ የቤቴስዳን፣ ቼቪ ቼዝ፣ ከንሲንግተን፣ እና ፖቶማክ ክፍሎችን ባካተተው በትምህርት ዲስትሪክት 3 ውስጥ መኖር አለበት/ባት። ዲስትሪክቱን ያካተቱ የተወሰኑ አከባቢዎች በሜሪላንድ የተብራራ ሕግ የትምህርት አንቀጽ 3-901 (f) (3) (VII) ውስጥ ይገኛል። ዲስትሪክቱን ያካተቱ የተወሰኑ አከባቢዎች በሜሪላንድ የተብራራ ሕግ አንቀጽ 3-901 (F) (3) (vii) ውስጥ ይገኛሉ። እንዲሁም የድስትሪክቱን ወሰኖች ለምርጫ ቦርድ በ 240-770-8500 በመደወል ሊታወቅ ይችላል። ለትምህርት ቦርድ ሥልጣን ተገዥ የሆነ/ች፣ ለምሳሌ የትምህርት ቤት ስርዓት ሠራተኛ፣ ማመልከት የሚችል/የምትችል ሲሆን ለክፍት የሥራ ቦታ እጩ ሊሆን/ልትሆን ይችላል/ትችላለች፣ ግን የቦርዱ አባል ሆኖ እንዲያገለግል/እንድታገለግል ከተመረጠ/ች ቦታውን መልቀቅ ይጠበቅበታል/ባታል።

ማመልከቻዎች በ 5:00 p.m. ኖቬምበር 5/2021 ላይ መድረስ አለባቸው። ስለ ክፍት ቦታው ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገዎት፣ እባክዎን ለትምህርት ቦርድ የሥራ ባልደረባ ወ/ሮ ሎሪ-ክሪስቲና ዌብ በ 240-740-3030 ይደውሉ። ግለሰቦች ሰነዶቹን ለትምህርት ቦርድ በፖስታ እንዲልኩ፣ በእጅ እንዲያስረክቡ ወይም ኢሜል እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ። የፖስታ አድራሻ፦ 850 Hungerford Drive, Room 123, Rockville, Maryland 20850። በኢሜይል የሚላኩ ማመልከቻዎች በ District3Vacancy@mcpsmd.org መቅረብ አለባቸው። የሁሉም አመልካቾች ስሞች እና ደብዳቤዎች ለሕዝብ ምልከታ ይፋ ይደረጋሉ።

ምደባ የሚፈልጉ ግለሰቦች የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው፦

  1. አመልካች ኖቬምበር 2022 እስከሚያበቃ ድረስ በትምህርት ቦርድ ላይ እንደ ዲስትሪክት 3 ተወካይ ሆኖ(ና) ለማገልገል ፈቃደኛነቱ(ቷ)ን የሚገልጽ የተፈረመ ደብዳቤ፣ እና አመልካቹ(ቿ) ለከፍተኛ የሥራ ጫና እና ጊዜ ለመስጠት ያለውን/ያላትን ቁርጠኝነት ግንዛቤ የሚገልጽ መግለጫ፤
  2. የአመልካቹ(ቿ) የግል ታሪክ እና አግባብነት ያለው ሲቪክ፣ ሙያዊ እና ሌላ ተሞክሮ አጭር መግለጫ (የትምህርትና የሥራ ልምድ ዝርዝር/resume ይያያዛል)፤
  3. አመልካቹ(ቿ) በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተመዘገበ(ች) እና በዲስትሪክት 3 ውስጥ የሚኖር/የምትኖር መሆኑን የሚያረጋግጥ መግለጫ። እና
  4. ለግንኙነት አመቺ የሆነ የኢሜል አድራሻ እና የስልክ ቁጥሮች የአመልካቹ(ቿ) የግንኙነት መረጃ ጭምር መቅረብ አለበት።